Loading...

አመታዊ ኮንፍራንሶች

አመታዊ ኮንፈረንስ

ሀሌሉያ ፌስቲቫል

“ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ለእግዚአብሔር ዘምሩ!”
መዝሙር 96:1

በክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን ፣ በፅዮን ድምፅ አገልግሎት በግንቦት ወር የሚዘጋጅ በአይነቱ ልዩ የሆነ ዓመታዊ ኮንፍራንስ ሲሆን ዓላማውም እግዚአብሔርን ስለ ታላቅነቱ፣ ገናናነቱ፣ ልዕልናው የምንወድስበት እንዲሁም ቅዱሳን ሁላችን እግዚአብሄር ያረገልንን ሁሉ በማስታወስ ጽፈን መተን ስለ እያንዳንዱ የአባታችን መልካምነት እና የማዳኑ ክንድ የምናመሰግንበት እግዚአብሄርንም በከበረ መንገድ የምናከብርበት ድንቅ ቀን ነው።

በዚህ ዕለት የህይወታችን አንደኛው እና ዋነኛው አካል እና መገለጥ የሆነውን የአምልኮን ህይወት እንዲሁም ለህይወታችን የብዙ በረከት ደጆች ምክኒያት የሆነውን የምስጋና ህይወት እንካፈል ዘንድ መልካሙን የእግዚአብሔርን ቃል እንማራለን በልዩ ልዩ የስነ-ጥበብ ስራዎች ደግሞ የፅዮንን የህይወት ስርዐት እንካፈላለን።

በአንድ ልብ እና መንፈስ ሆነን ለክብር ንጉስ ሀሌሉያ እንል ዘንድ ተቀላቀሉን!

አመታዊ ኮንፈረንስ

የመንግስቱ ፕሮቶኮል ኮንፈረንስ

በክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን ፤ በመንግስቱ ፕሮቶኮል አገልግሎት ነሃሴ ወር ላይ የሚዘጋጅ በአይነቱ ልዩ የሆነ ዓመታዊ ስብሰባ ሲሆን ዓላማውም ቅዱሳንን በእግዚአብሄር መንግስት የግንኙነት ጥበቦች ማስታጠቅ ነው።

አመታዊ ኮንፈረንስ

የቤዛነት ኮንፈረንስ

በክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን ከቤዛነት አገልግሎት ጋር በመሆን በየካቲት ወር የሚደረግ አመታዊ ኮንፍረንስ ሲሆን የአገልግሎት ራእይም ድሆችን ለክብር መቤዠት የሚል እንደመሆኑ የኮንፍረንሱ ዋና አላማም ቅዱሳን ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች እንዲኖሩ ረዳት ወይንም ጥላ አድርጎ ማስነሳት ነው።

አመታዊ ኮንፈረንስ

የመንግስቱ ፋይናንስ ኮንቬንሽን

በክራይስት ሲቲ ቸርች፤ በመንግስቱ ባለጠግነት አገልግሎት በህዳር ወር ላይ የሚዘጋጅ በአይነቱ ልዩ የሆነ ዓመታዊ ስብሰባ ሲሆን ዓላማውም ቅዱሳንን በእግዚአብሄር መንግስት የፋይናንስ ጥበቦች ማስታጠቅ ነው።