ህብር ያለው የመንፈስ አንድነት እና ያማረ ሰላም በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ቅዱሳን መካከል ማየት
'ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!'
መዝሙር 133:1
የመንግስቱ ፕሮቶኮል አገልግሎት ዳይሬክተር
ህብር ያለው አንድነት እና ያማረ ሰላም በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ቅዱሳን መካከል ማየት ነው።
ትክክለኛ አካሄድን የሚያሳዩ የደንብ ስርዓቶችን እና ፕሮቶኮሎችን በማጽናት፤ በቅዱሳን ሁሉ መካከል የተቀደሱ ግንኙነቶችን መመስረት እና መገንባት ነው።
የመንግስቱን ክብር እንድናበራ፤ የእግዚአብሄር በረከት እና ሕይወት ወደ ቅዱሳኑ ሁሉ እንዲፈስ ማድረግ
ፕሮቶኮል “Protokollon” (ፕሮቶኮሎን) ከሚል ከቀድሞ የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን “Proto-“ ማለት “First” (ቀዳሚ፣ ፊተኛ፣አንደኛ፣ መጀመሪያ) ማለት ሲሆን “kolla” ማለት ደግሞ “glue” (ማሸጊያ፣ ማጣበቂያ፣ ሙጫ) የሚል ትርጉም ይይዛል፡፡ ይህም የመጀመሪያ ከፊት የሚገኝ ማሸጊያ እንደማለት ሲሆን በቀድሞ ዘመን በእጅ በሚጻፉ የብራና መጻሕፍት በፊተኛው ገጽ ላይ የተጻፉበትን ቀን እና የመጻሕፍቱን ይዘት የሚገልጽ በማጣበቂያ (glue) የሚያያዙ የብራና ጽሁፎች ይዘጋጁላቸው ነበር እነርሱንም ጽሁፎች “Protokollon” (ፕሮቶኮሎን) በማለት ይጠሯቸው ነበር፡፡ ከዚህም በመቀጠል በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጽሐፍቶችን መቅድም እና ሰዎች የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉባቸውን የጽሁፍ መዝገቦች ፕሮቶኮል በማለት ይጠሯቸው ነበር።
በመጨረሻም ከ19ኛው መቶ ክፍለዘመን ጀምሮ፤ የፈረንሳይ የሐገር መሪዎች ከተከበሩ ባለስልጣናት ጋር ለሚያደርጓቸው አከባበሮች (Ceremonies) እና ግንኙነቶች (Relations) ሊከተሏቸው የሚገቡትን ሥነ-ስርዓቶች ለመግለጽ ፕሮቶኮል የሚለውን ቃል መጠቀም ጀመሩ። ይህንኑ ተመሳሳይ ጽንሰ ሐሳብ በመያዝ ማንኛውንም አግባብነት ያላቸውን የግንኙነት ደንቦች (Code) ለመግለጽ፤ ፕሮቶኮል የሚለው ቃል እስከአሁን ድረስ ዘልቋል።
ፕሮቶኮል ግንኙነቶችን የመገንባት እና በግንኙነቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላት ከግንኙነቱ አዎንታዊ ውጤት እንዲያገኙ የሚያስችል ጥበብ ነው። ፕሮቶኮል ግንኙነት የመፍጠር፣ የመገንባት፣ የመንከባከብ፣ የመጠበቅ እና አላስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የመስበር ጥበብ ነው።
ፕሮቶኮል በታላላቆች ፊት ሞገስ እና ክብር የሚሰጥ ታላቅ ጥበብ ነው፡፡ በነገስታት፣ በኃያላን፣ በታላላቆች ፊት ያቆማል።
ፕሮቶኮል ልብን የመማረክ ጥበብ ነው።
የእግዚአብሄር መንግስት ቅዱሳኑን በበረከት እና በሕይወት ለመሙላት ከዚህ ዓለም ስርዓት ፍጹም በተለየ ሁኔታ ያዘጋጃቸው የተቀደሱ የግንኙነት ፕሮቶኮሎች አሉት፡፡
የመንግስቱ ፕሮቶኮሎች የስልጣን፣ የኃይል፣ የበረከት፣ የብልጽግና፣ የሞገስ፣ የክብር፣ የከፍታ፣ የታላቅነት እና የስኬት ምስጢራዊ ቁልፎች ናቸው፡፡
ቅዱሳን ሁሉ በሶስት የተለያዩ ሰፊ የግንኙነት ክልሎች (realm) ውስጥ በምድር ላይ በሚኖሩበት የሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይመላለሳሉ፡፡
1ኛ የእግዚአብሄር መንግስት (ቤተክርስቲያን)፣ 2ኛ ቤተሰብ እና 3ኛ ዓለም (የዓለም መንግስት) ናቸው ፡፡
ሶስቱም የግንኙነት ክልሎች በውስጣቸው በርካታ በአይነታቸው የተለያዩ የግንኙነት ዓይነቶችን የያዙ ሲሆን እያንዳንዳቸው ደግሞ ልዩ ልዩ የሆኑ ፕሮቶኮሎችን የሚከተሉ ናቸው፡፡
እነዚህ የተለያዩ የግንኙነት ፕሮቶኮሎች ደግሞ በእያንዳንዱ የግንኙነት አይነቶች ውስጥ እግዚአብሄር ለክብራችን ያስቀመጣቸውን በረከቶች የምንቀበልባቸው ምስጢራዊ ቁልፎች ናቸው፡፡
ለምሳሌ ቤተሰብ ውስጥ በወላጆች እና በልጆች መካከል ሊኖር ስለሚገባ አንድ የግንኙነት አይነት ብንመለከት የእግዚአብሄር ቃል በኤፌሶን 6:2-3 ላይ “መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።’ በማለት ያስተምረናል፡፡
ህብር ያለው አንድነት እና ያማረ ሰላም በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ቅዱሳን መካከል ማየት
ህብር ያለው አንድነት እና ያማረ ሰላም በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ቅዱሳን መካከል ማየት
ህብር ያለው አንድነት እና ያማረ ሰላም በቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ቅዱሳን መካከል ማየት
............
በክራይስት ሲቲ ቸርች፤ በመንግስቱ ፕሮቶኮል አገልግሎት ነሃሴ ወር ላይ የሚዘጋጅ በአይነቱ ልዩ የሆነ ዓመታዊ ስብሰባ ሲሆን ዓላማውም ቅዱሳንን በእግዚአብሄር መንግስት የግንኙነት ጥበቦች ማስታጠቅ ነው።