Loading...

የመንግስቱ ተልዕኮ አገልግሎት

Kings Ministry Logo

ራዕይ

የመንግስቱ መልእክት ለአለም ሁሉ ደርሶ : ትውልዱ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሲፈልስ ማየት

ቅዱሳን በአለማቸው የመንግስቱ ቃል መልእክተኞች እና የክርስቶስ እንደራሴዎች ሆነው ማየት


ለሕዝብ ሁሉ ምስክር እንዲሆን፣ ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።

ማቴ 24:14

MOG Abenezer

የእግዚአብሔር ሰው አቤኔዘር ማርቆስ

የመንግስቱ ተልዕኮ አገልግሎት ዳይሬክተር

ራዕይ

የመንግስቱ መልእክት ለአለም ሁሉ ደርሶ : ትውልዱ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሲፈልስ ማየት


ቅዱሳን በአለማቸው የመንግስቱ ቃል መልእክተኞች እና የክርስቶስ እንደራሴዎች ሆነው ማየት

ተልዕኮ

የመንግስቱ ቃል መንፈስን እና ኃይልን በመግለጥ ለትውልዱ ሁሉ መስበክ እና ማስተማር


ቅዱሳን ነፍሳትን የሚማርክ የነገስታት ልብ እና ሰውን ከእግዚአብሔር የሚያስታርቅ የካህናት እንዲኖራቸው ማስታጥቅ

ዓላማ

ሰዎች ሁሉ ከጨለማ ስልጣን እና ከሚመጣው ፍርድ አምልጠው የእግዚአብሔር መንግስት ወራሾች እንዲሆኑ


ቅዱሳን በዓለማቸው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን የማስታረቅ አገልግሎት እንዲፈጽሙ

እሴት

  • የመንግስቱ ወንጌል
  • ነፍሳትን መማረክ
  • የማስታረቅ አገልግሎት
  • ምልጃ
  • መስዋዕትነት
  • የክርስቶስ ፍቅር
  • መንፈስ እና ኃይልን መግለጥ
ወደ ዓለም


ማቴ 24:14 "ለሕዝብ ሁሉ ምስክር እንዲሆን፣ ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።"

ወደ ቅዱሳን


ማቴ 24:14 "ለሕዝብ ሁሉ ምስክር እንዲሆን፣ ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።"

የመንግስቱ ተልዕኮ

መሠረቶች

የእግዚአብሔር መንግስት

የእግዚአብሔር መንግስት

በመንፈስ ዓለም የሰው ልጆችን እየገዙ ያሉ ሁለት መንግስታት አሉ። አነርሱም የእግዚአብሔር መንግስት እና የሰይጣን መንግስት ናቸው። የሁለቱም መንግስታት ሐሳብ እና ዓላማ በሚገዙት ሕዝብ የሕይወት ስርዓት ይታያል። የእግዚአብሔር መንግስት የሕይወት መገለጥ ጽድቅ እና ሰላም በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ ሲሆን የሰይጣን መንግሰት የሕይወት መገለጥ ደግሞ ዓመጻ፣ ኃጢያት፣ ሞት፣ ሐዘን፣በሽታ፣ ባርነት እና ጥፋት ነው። የእግዚአብሔር መንግስት ጌታ እና ንጉስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ገዢነት የሚተዳደር የብርሃን መንግስት ሲሆን የሰይጣን መንግስት በሰይጣን እና በመላዕክቱ ገዢነት የሚተዳደር የጨለማ መንግስት ነው። የእግዚአብሔር መንግስት ለዘላለም ጸንቶ የሚኖር ሲሆን የሰይጣን መንግስት ግን በፍርድ ለዘላለም ጥፋት የተወሰነ መንግስት ነው። መንሹ በእጁ የሆነው ጌታ በፍርድ ቀን አውድማውን ሲያጠራ ስንዴውን (የእግዚአብሄርን ልጆች) ከእንክርዳዱ (ከዲያብሎስ ልጆች) ይለያል። ስንዴውን ወደ ጎተራው (ወደ ዘላለማዊ መንግስቱ እና ሐገሩ) እንክርዳዱን ወደ ማይጠፋ እሳት (ወደ ዘላለም እሳት ፍርድ) ይከታቸዋል። አሁን ያለንበት ዘመን፤ እግዚአብሔር በምሕረቱ እና በጸጋው ሰዎች ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የኃጢአትን ስርየት ተቀብለው የእግዚአብሔርን መንግስት መውረስ የሚችሉበት፤ የንስሐ እና የምሕረት ዘመን ነው። የዚህም አገልግሎት ዋነኛ ተልዕኮው ሰዎችን ከጨለማ አገዛዝ በእግዚአብሔር ኃይል ነጻ እያወጡ ከፍርድ እና ከሚመጣው ቁጣ አምልጠው ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት እንዲፈልሱ ማድረግ ነው። እግዚአብሔር መንግስት እንጂ ኃይማኖት የለውምና፤ የሰማያዊ መንግስት እንጂ የኃይማኖት ተልዕኮ የለንም።

የመንግስቱ ወንጌል

የመንግስቱ ወንጌል

"ለሕዝብ ሁሉ ምስክር እንዲሆን፣ ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።" ማቴ 24:14

ወንጌል የሚለው ቃል መሰረቱ 'ዩጌልዮን' ከሚል የግሪክ ቃል የወጣ ሲሆን፤ ትርጉሙም መልካም ዜና ወይም የምስራች ማለት ነው፡፡ የመንግስቱ ወንጌል ስንል ደግሞ የምስራቹ፤ መንግስቱ (የእግዚአብሔር መንግስት) ነው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር መንግስት ለሰዎች ሁሉ ሊነገር የሚገባው ታላቅ የምስራች ነው። ምክንያቱም የዘላለም እሳት ከተፈረደበት ከጨለማ አገዛዝ አምልጠን፤ ልንድንበት የምንችልበት፤ ኃይል ያለው፥ ሊታደገን የሚችል ሌላ መንግሥት የለምና። መንግስቱን ለመውረስ ብቁ የሚያደርገንን የኃጢያት ስርየት፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቀን እና በመንፈስ ቅዱስ ማህተም ታትመን፤ በጸጋው የመንግስቱ ወራሽ ሆነናል። ይህ ለሰዎች ሁሉ በነጻ የተዘጋጀ የእግዚአብሔር የፍቅር ስጦታ ነው።

"እርሱ ከጨለማ አገዛዝ ታደገን፤ ወደሚወደው ልጁ መንግሥትም አሻገረን፤ በእርሱም መዋጀትን በደሙ አግኝተናል፤ ይህም የኃጢያት ይቅርታ ነው።" ቆላ 1፡13-14

እግዚአብሔር ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት ያስገባን፤ ስለሚወደንና ለእኛ ከዚህ ሌላ የተሻለ ስፍራ ስለሌለው ነው፡ የልጁ መንግስት ኢየሱስ ክርሰቶስ ንጉስና ጌታ ሆኖ የሚገዛበት መንግስት ነው። ስለ ኢየሱስ አገዛዝና ንግስና መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር

"በመጀመሪያ ስሙ "የጽድቅ ንጉስ" ማለት ነው፤ ኋላም ደግሞ "የሳሌም ንጉስ" ማለትም "የሰላም ንጉስ" ማለት ነው፡፡" ዕብ 7፡-2