ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በሚኖረን ልዩ: የፀሎት ፣ የአምልኮ ፣ የምስክርነት እና የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት ጊዜ ላይ ተገኝተው አብረውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ እና የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጋብዘኖታል፤ እርሶም ሌሎችን ይጋብዙ!
ዘወትር ማክሰኞ በምናደርገው የፆም እና የፀሎት ጊዜ ከማለዳ 12:00 ጀምሮ በቴሌግራም ገፃችን በመገኘት አብረውን ይፀልዩ ፤ የበረከቱ ተካፋይም ይሁኑ!
ዘወትር ቅዳሜ ከማለዳ 4:00 እስከ 6:00 ስላልዳኑ ነፍሳት ፣ ለቤተሰቦቻችን እና በዙሪያችንም ስላሉት ሁሉ የምንማልድበት ልዩ የምልጃ ጊዜ በመንግስቱ ተልዕኮ አገልግሎት አዘጋጅነት!
"ይህ በእግዚአብሔር በአዳኛችን ፊት ደስ የሚያሰኝ ነው.. እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል።
1 ጢሞቴዎስ 2:3-4
በወሩ የመጀመሪያ እሁድ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ልዩ የሆነ የፀሎት ፣ የአምልኮ ፣ የመስዋዕት ፣ የምስክርነት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት እና የጌታን እራት የምንወስድበት ጊዜ ይኖረናል። እርሶም በክብር ተጋብዘዋል!
እሁድ ከ4:30 ጀምሮ የመንግስቱ ዘሮች የአገልግሎት ክፍል ልጆችን በእግዚአብሔር ቃል እውነት እያስታጠቀ ይገኛል። ልጆችዎ በእግዚአብሔር ቃል እውነት መንገዳቸው እንዲቃና ፣ ፍፃሜያቸው የከፍታ እና የክብር እንዲሆን ይዘዋቸው ይምጡ።
በሳምንቱ ቀናቶች ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የንጉሡ ቤተሰብ ስብሰባዎች ይደረጋሉ። በእነዚህ ስብሰባዎች ውስጥ የፀሎት ፣ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ፣ የወንጌል ስርጭት እና የምስጋና ጊዜ ይኖረናል። እርሶም የንጉሱ ቤተሰብ አባል ካልሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ።
በቤተክርስቲያን የነገስታት አገልግሎት የተዘጋጀ የባስ አገልግሎት ይሄ የባስ አገልግሎት ለእሁድ የአምልኮ ጊዜ ከ4ቱም የአዲስ አበባ አቅጣጫዎች የሚነሳ እና በ2 ዙር (ጠዋት 2:00 እና 4:00 በሚደርስ) ቅዱሳንን ወደ ቤተክርስቲያን የሚያደርስ እንዲሁም የሚመልስ ይሆናል። የዚህ የባስ አገልግሎት አጋር በመሆን ለቅዱሳን በረከት እንዲሆኑ ግብዛችንን ለማቅረብ እንወዳለን።