ድሆችን/ችግረኞችን/ ለክብር መዋጀት
ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
የያዕቆብ መልእክት 1:27
የቤዛነት አገልግሎት ዳይሬክተር
ድሆችን/ችግረኞችን/ ለክብር መዋጀት
ለደሀአደጎች፣ ለመበለቶች፣ ለመጻተኞች ጥላ የሚሆኑ ቅዱሳንን ማስነሳት
ለቅዱሳን ለመንፈሳዊ ህይወት እድገትና ለውጥ በር/ደጅ/ መሆን
Need/ፍላጎትን/ በሟሟላት መንፈሳቸውን መድረስ
በቤተክርስቲያን ለሚገኙ ቅዱሳን የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ በማድረግ እና ጉድለታቸውን በመሙላት ከጎናቸው በመቆም በመንፈሳዊ ህይወታቸው እንዲያድጉ የሚረዳ እንዲሁም የተለያዩ ክህሎቶችን ያዳብሩ ዘንድ የሚረዳ ስልጠና የሚሰጥ የአገልግሎት ክፍል ነው።
ቤተክርስቲያን ወይም ቅዱሳን በተለያዩ የማህበረሰብ ተኮር ጉዳይ ላይ እንዲሁም በማህበራዊ እና በአገር አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከመንግስት እና ከተለያዩ በጎ አድራጊ ተቋማት ጋር አብሮ የሚሰራ የአገልግሎት ክፍል ነው።
በክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን ከቤዛነት አገልግሎት ጋር በመሆን በየካቲት ወር የሚደረግ አመታዊ ኮንፍረንስ ሲሆን የአገልግሎት ራእይም ድሆችን ለክብር መቤዠት የሚል እንደመሆኑ የኮንፍረንሱ ዋና አላማም ቅዱሳን ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች እንዲኖሩ ረዳት ወይንም ጥላ አድርጎ ማስነሳት ነው።