Loading...

የእረኝነት ክትትል አገልግሎት

Kings Ministry Logo

ራዕይ

ቅዱሳን በመንግስቱ ጸንተው እና አብበው ማየት

MOG Abenezer

ሐዋርያ ቅዱስ ተካልኝ

የእረኝነት ክትትል አገልግሎት ዳይሬክተር

ራዕይ

ቅዱሳን በመንግስቱ ጸንተው እና አብበው ማየት

ተልዕኮ

ቅዱሳንን ለመንግስቱ ሕይወት መመገብ፣ ማሰማራት፣ መላክ

ዓላማ

የሰማያዊ መንግስትን ሕይወት እና ክብር መግለጥ

እሴት

  • የመንግስቱ ትምህርት
  • ማማከር
  • መማለድ
  • መንከባከብ
  • ክትትል እና ጉብኝት
  • ለመንጋው ምሳሌ መሆን
  • ማስተዳደር
የእረኝነት ክትትል አገልግሎት ክፍል


ቅዱሳንን ለመንግስቱ ሕይወት መመገብ፣ ማሰማራት፣ መላክ

Hill Zion landscape for Kings Ministry
ሂል ዛየን የመሰረት ትምህርት ቤት


የቅዱሳን ልብ በእግዚአብሔር መንግስት ቃል ተመስርቶ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን ሲመላለሱ ማየት

በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ። ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው። ‘ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን’ ይላሉ። በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ። ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም። እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፥ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ

ኢሳይያስ 2:2 - 5

ስልት

ቅዱሳንን እንደ መንፈሳዊ የእድገት ደረጃቸው በእግዚአብሔር መንግስት ቃል መገንባት

እሴት

  • የመንግስት ቃል
  • የመንፈሳዊ እድገት ደረጃዎችን መለየት
  • ድግግሞሽ
  • ቀላል የመማር ማስተማር ሂደት
  • ክትትል እና ምዘና

የመንፈሳዊ የእድገት ደረጃዎች

የመንፈሳዊ የእድገት ደረጃዎች

የእግዚአብሔር ቃል የቅዱሳንን የመንፈሳዊ የእድገት ደረጃዎች በሶስት ይከፍላቸዋል። እነርሱም ልጅነት፣ ጉብዝና እና አባትነት ናቸው። እነዚህ የመንፈሳዊ እድሜ ክልሎች የየራሳቸው የሆነ ልዩ ባህሪያት እና መገለጫዎች ያላቸው ሲሆን ቅዱሳን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ዳግም በመወለድ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ በእነዚህ የመንፈሳዊ የእድሜ ክልሎች ውስጥ በደረጃ ከአንዱ ወደ አንዱ ማለፋቸው ግድ ነው።

ከአንዱ የመንፈሳዊ እድሜ ክልል ወደ ሚቀጥለው ለመሻገር፤ በቅዱሳን ልብ ውስጥ በእግዚአብሔር መንግስት ቃል ሊገነቡ የሚገባቸው ልዩ መሰረቶች ያስፈልጋሉ። ለምሳሌ በመንፈስ ልጆች ወይም ህጻናት የሆኑ ቅዱሳን ወደ ጉብዝና እንዲሻገሩ በልባቸው መገንባት ያለበት የጎበዞች መሰረት አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ጎበዞችን ወደ አባትነት ለማሳደግ በጎበዞች ልብ ውስጥ መገንባት ያለበት የአባቶች መሰረት አለ። በመጨረሻም አባቶች የሚያፈሩት የፍሬ መጠን የሚወሰነው፤ በልባቸው በሚገነባው ልዩ የእግዚአብሔር መንግስት ቃል መሰረት ላይ ነው።

Spiritual Development
...

ስለዚህ የ Hill Zion Foundation School ስልታዊ አካሄድ መሰረቱን ያደረገው በሶስቱ የመንፈሳዊ እድገት ደረጃዎች ላይ ሲሆን ትምህርቶቹም በሶስት ክፍሎች እና የተለያዩ ስርዓተ ትምህርቶች (Curriculum) የተከፋፈለ ነው።

1. የመሰረት ትምህርት አንድ (Foundation Class I) - የዜጎች/የአማኞች መሰረት

2. የመሰረት ትምህርት ሁለት (Foundation Class II) - የካህናት/የአገልጋዮች መሰረት

3. የመሰረት ትምህርት ሶስት (Foundation Class III) - የነገስታት/የመሪዎች መሰረት

እድገት ጤናማ ተፈጥሮአዊ የሕይወት ለውጥ ነው። በአንጻሩ ደግሞ አለማደግ ከፍተኛ የጤና ችግር እና አልፎም ለሞት የሚያበቃ ነገር ነው። የመንፈሳዊ እድገት ደረጃዎችን እና ባህሪያቶቻቸውን ማወቅ፥ በክርስቶስ በሆነው ሕይወት ያለንበትን የመንፈሳዊ እድሜ ክልል በሚገባ ለመለየት እና ከልጅነት ወደ አባትነት ለማደግ የሚረዱንን ተገቢ እርምጃዎች ለመውሰድ የሚረዳ ብርሃን ነው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ልጆቹ ያለው የፍቅር ዓላማ፥ የልጅነትን ጠባይ እየሻርን ከፍተኛ ወደሆነው፣ ለሌሎች በረከት ወደምንሆንበት፣ ሕይወታችንን እግዚአብሔር ለእኛ ባለው ሰማያዊ ራዕይ እና ዓላማ ወደምንመራበት እና በመንግስቱ ውስጥ ለብዙዎች ጥላ ወደምንሆንበት ወደ አባትነት የመንፈሳዊ እድገት ደረጃ እንድንደርስ ነው። ይህ የመንፈሳዊ እድገት ደረጃ ለተወሰኑ ቅዱሳን የተዘጋጀ ስጦታ ሳይሆን ለሁሉም ልጆቹ የታለመ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ወደዚህ ክቡር ፍጻሜ የምትደርሱበት ጥበብ እና ጸጋ ይብዛላችሁ!

Foundation Class I Foundation Class II Foundation Class III
የመንግስቱ ዘሮች አገልግሎት


የሰማያዊ መንግስትን ሕይወት እና ክብር መግለጥ

የጋብቻ እና ትዳር ማማከር


ቅዱሳንን ለመንግስቱ ሕይወት መመገብ፣ ማሰማራት፣ መላክ