Loading...

እንኳን ደህና መጡ!

የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን

. . . የፍቅሩ ልጅ መንግስት

የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን

Church Leader

ራዕይ

የመንግስቱን መልዕክት ለትውልድ ሁሉ ማድረስ የሰማያዊ መንግስትን ሕይወት እና ክብር መግለጥ


ተልዕኮ

መንፈስን እና ኃይልን በመግለጥ ለትውልዱ የመንግስቱን ቃል መስበክ እና ማስተማር

ቤተክርስቲያንን እንደ ሰማያዊ ከተማ በመመስረት እና በመገንባት፤ ቅዱሳንን እንደ ነገስታት እና ካህናት ማሳደግ እንዲሁም እንደ ሰማያዊ ሕዝብ ማስነሳት

Church Leader

ሐዋርያ ቅዱስ ተካልኝ

የክርስቶስ ከተማ ቤተክርስቲያን መሪ እና የራዕይ ባላደራ

የጋራ

መደበኛ ፕሮግራሞቻችን

የእሁድ አምልኮ ጊዜ

ዘወትር እሁድ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ በሚኖረን ልዩ: የፀሎት ፣ የአምልኮ ፣ የምስክርነት እና የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት ጊዜ ላይ ተገኝተው አብረውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ እና የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጋብዘኖታል፤ እርሶም ሌሎችን ይጋብዙ!

Sunday Service
የቀጥታ ስርጭት የፀሎት ጊዜ

ዘወትር ማክሰኞ በምናደርገው የፆም እና የፀሎት ጊዜ ከማለዳ 12:00 ጀምሮ በቴሌግራም ገፃችን በመገኘት አብረውን ይፀልዩ ፤ የበረከቱ ተካፋይም ይሁኑ!

Fasting Prayer
ስለነፍሳት የሚደረግ ምልጃ

ዘወትር ቅዳሜ ከማለዳ 4:00 እስከ 6:00 ስላልዳኑ ነፍሳት ፣ ለቤተሰቦቻችን እና በዙሪያችንም ስላሉት ሁሉ የምንማልድበት ልዩ የምልጃ ጊዜ በመንግስቱ ተልዕኮ አገልግሎት አዘጋጅነት!

"ይህ በእግዚአብሔር በአዳኛችን ፊት ደስ የሚያሰኝ ነው.. እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል።

1 ጢሞቴዎስ 2:3-4

Fasting and Prayer
ልዩ የእሁድ ፕሮግራም (Super Sunday)

በወሩ የመጀመሪያ እሁድ ከጠዋቱ 4:00 ጀምሮ ልዩ የሆነ የፀሎት ፣ የአምልኮ ፣ የመስዋዕት ፣ የምስክርነት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የምንማርበት እና የጌታን እራት የምንወስድበት ጊዜ ይኖረናል። እርሶም በክብር ተጋብዘዋል!

Fasting Prayer
የመንግስቱ ዘሮች

እሁድ ከ4:30 ጀምሮ የመንግስቱ ዘሮች የአገልግሎት ክፍል ልጆችን በእግዚአብሔር ቃል እውነት እያስታጠቀ ይገኛል። ልጆችዎ በእግዚአብሔር ቃል እውነት መንገዳቸው እንዲቃና ፣ ፍፃሜያቸው የከፍታ እና የክብር እንዲሆን ይዘዋቸው ይምጡ።

Fasting and Prayer
የንጉሱ ቤተሰብ ስብሰባ

በሳምንቱ ቀናቶች ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የንጉሡ ቤተሰብ ስብሰባዎች ይደረጋሉ። በእነዚህ ስብሰባዎች ውስጥ የፀሎት ፣ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ፣ የወንጌል ስርጭት እና የምስጋና ጊዜ ይኖረናል። እርሶም የንጉሱ ቤተሰብ አባል ካልሆኑ አሁኑኑ ይመዝገቡ።

Fasting Prayer
የቤተክርስቲያን የባስ ትራንስፖርት አገልግሎት

በቤተክርስቲያን የነገስታት አገልግሎት የተዘጋጀ የባስ አገልግሎት ይሄ የባስ አገልግሎት ለእሁድ የአምልኮ ጊዜ ከ5ቱም የአዲስ አበባ አቅጣጫዎች የሚነሳ እና በ2 ዙር (ጠዋት 2:00 እና 4:00 በሚደርስ) ቅዱሳንን ወደ ቤተክርስቲያን የሚያደርስ እንዲሁም የሚመልስ ይሆናል። የዚህ የባስ አገልግሎት አጋር በመሆን ለቅዱሳን በረከት እንዲሆኑ ግብዛችንን ለማቅረብ እንወዳለን።

Fasting and Prayer
ያግኙን

በሚከተሉት አማራጮች ሊያገኙን ይችላሉ